በዲማ ወረዳ የዲጂታል መረጃ አያያዝ ሲስተም/AI-integrated Party management system/ የተሰኘ ሶፍትዌር ተዋወቀ *************** ከዲማ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (ሚያዚያ 8/2018 ዓ.ም) የዲማ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት እና የወረዳው ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት በጋራ ያበለፀጉት የዲጂታል መረጃ አያያዝ ሲስተም/AI-integrated Party management system/ የወረዳው አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተዋውቋል ። መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የዲማ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ኡኬሎ ኡጁሉ እንደገለፁት ጤንነቱን የጠበቀ መረጃ ቋት ለፓርቲያችን ሆነ ለሌሎች ተቋማት አስፈላጊ በመሆኑ ዛሬ የመጀመሪያ የሆነ ዲጂታል የመረጃ አያያዝ ሲስተም/AI-integrated Party management system/ አበልፅገን ስናስጀምር የፓርቲያችን የ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ አካል ነው ብለዋል ። የወረዳው ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ሃላፊ የሆኑት አቶ ኡጁሉ ቻም በበኩላቸው የሁሉም የልማት መስኮች መነሻ የሆነውን መረጃ በአግባቡ ሰንዶ መያዝ ለሀገር እድገትና ደህንነት ያለው ሚና ወሳኝ በመሆኑ ዛሬ ያስተዋወቅነው ሶፍትዌር ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ስራን ለማቀላጠፍ እና የፓርቲው አመራር አባላት እንዲሁም የወረዳው ማህበረሰብ የፈለገውን አስተያየት በነፃነት እንዲሰጥ የሚጋብዝ መሆኑን ተናግሯል ። ሶፍትዌሩን ያለሙት የHOME-Tech solution ስራ አስኪያጅ አቶ እንድሪስ ኢሳ የሶፍትዌሩን ስራዎች ባስተዋወቁበት ጊዜ እንደገለፁት ይህ ሶፍትዌር የፓርቲውን አጠቃላይ ስራዎችን በአንድ አቀናጅቶ የያዘና ለአጠቃቀም ቀላል መሆኑን ተናግረዋል ። በቀጣይም ስለ ሶፍትዌሩ አጠቃቀምና ተያያዥ ጉዳዮች ተከታታይ ስልጠና እንደሚሰጥም በመድረኩ ተገልፀዋል ።