የዲማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ*************** ከዲማ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (ሚያዚያ 3/2018 ዓ.ም) የዲማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጊሎ ኡሞድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል ። ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው ፤ ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ዘላለማዊ የሞት መጋረጃን ከማስወገዱም ባሻገር በምድር ላለን የሰው ልጆች ሁሉ ፍቅርን ፣ ትህትናን፣ መልካምነትንና ለሌሎች መስዋዕትነት መክፈልን አስተምሮናል ብለዋል።
የዲማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ*************** ከዲማ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (ሚያዚያ 3/2018 ዓ.ም) የዲማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጊሎ ኡሞድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል ። ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው ፤ ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ዘላለማዊ የሞት መጋረጃን ከማስወገዱም ባሻገር በምድር ላለን የሰው ልጆች ሁሉ ፍቅርን ፣ ትህትናን፣ መልካምነትንና ለሌሎች መስዋዕትነት መክፈልን አስተምሮናል ብለዋል። ለዚህም ህዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ሲያከብር ለተቸገሩ ወገኖች የተለመደው የመረዳዳትና የመተጋገዝ ባህሉን በማጠናከር በአብሮነት መንፈስ በዓሉ ሊያሳልፍ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ። ዋና አስተዳዳሪው አክለውም በወረዳችን ራስን በምግብ ለመቻልና ከተረጂነት ለመላቀቅ የጀመርናቸውን አበረታች ስራዎች በማስቀጠል፤ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ በምናደርገው ጥረት መላው የወረዳችን ነዋሪዎች እንደተለመደው ከጎናችን በመሆን በሁሉም አቀፍ የልማት ተግባራት በመሳተፍ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል :: በመጨረሻም በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ዋና አስተዳዳሪው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል ።